ድንበር የሌለው ዲክታቶር ይሉሃል ይሄ ነው ፣ ድንበር ዘለል ዲክታቶር
ኢሳያስ ኤርትራ ውስጥ እንደሚያደርገው፣ በኬንያ ጉባኤ ላይ እውነተኛ ቀለሞቹን አሳይቷል (ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ)። ሰዉዬው እራሱን በጣም አዋቂ እንደሆነ አድርጎ ነው የሚያየው። ነገር ግን በኮንፈረንሱ ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንቶች፣ ኤርትራዊያን በብዛት አገራቸውን ለቀው እየተሰደዱ መሆናቸውን የሚረዱት በኢሳያስ የተሳሣተ ውይም ጎዶሎ አመለካከት ስለመሆኑ ግን ኢሰያስ አይረዳዉም። ፕሬዝዳንታችን የምንለው ሰው እንግዲህ ይህንን ሰው ነው።
ምንም እንኳን በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ኣላዋቂ ቢሆንም፣ ከትምህርቱ ውስንነት የተነሳ እራሱን ከፍ አድርጎ ማየቱ ኣይገርምም። ይህንን መቀበል ባይወድም በዓለም ብዙ ጉዳዮች ላይ ጠባብ እይታ ነው ያለው። ትዕቢተኛ ስለሆነ ደሞ አማካሪዎቹን መስማት እንኳን አይወድም። በጠቅላይ ሚኒስትሮች እና ፕሬዝዳንቶች ፊት ቀርቦ ጥሩ እውቀት ያለው ይመስል ሲዘባርቅ ማየቱ እንዴት ያሳፍራል። የእሱ ዓለም እንደ የአንድ ሰው ማራቶን ኮርስ ነው፣ አሸናፊው ደሞ ሁልጊዜም እራሱ ብቻ ነው። ብቻዉን የሚሮጥ የሚቀድመው የለም እንደሚባለው።
በቅርቡ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ለመቅረብ ባደረገው ሙከራ፣ ሰዎች እውቀቱ ዝቅ ያለ መሆኑን እንዲገነዘቡ አስችሎዋል። ከጓደኞቹ እና ከጥቂት ባልደረቦቹ የሰበሰበውን ዕውቀት ያለማቋረጥ እየወረወረ፣ ጎበዝ መባልን መርጦዋል ፣ እናም ያየተደበቀው ቂልነቱ ለአለም መገለጥ ጀምሯል።
በኮንፈረንሱ የግል ድርጅትን ጽንሰ ሃሳብ በመቃወም፣ የነጻነት መንገድ በመንግስት ቁጥጥር ብቻ የሚረጋገጥ ስለመሆኑ ለማሳየት ሞክሯል። ይህ ሰው በማይታመን ሁኔታ ታሟል ብንል ማጋነን ኣይሆንም። በኮንፈረንሱ ላይ “ማተኮር አለብን, ማተኮር አለብን, እሺ.” የጉባኤው የተጋባው ስለአየር ንብረት ለመነጋገር ነው። የጉባኤውን አጀንዳ እንኳን አላከበረም። የመናገር እድል ሲያገኝ ደካማ አመራሩን እና በኤርትራ እና በኤርትራውያን ላይ ያደረሰውን ጉዳትና ጸጸቱን ለማስረዳት ብቻ ይሞክራል። የእብሪት ባህሪው ደረቅ ስለሚያደርገው ደሞ በስህተት ላይ ስህተት መሥራቱን ቀጥሎዋል። ከሌሎች ለመማር እንዴት መሞከር እንዳለበት እንኩዋን አያውቅም ወይም ማወቅ አይፈልግም። ይህ ሰው በኤርትራ ውስጥ ተቃዋሚዎቹን በመግደል እና በማሰር ይታወቃል። በኤርትራ ውስጥ እንዳደረገው የኬንያ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች አመለካከታቸዉን ለማደናቀፍ መሞከሩ ደግሞ ይገርማል። ድንበር የሌለው ዲክታቶር ይሉሃል ይሄ ነው። በነዚህ ብዙ በሚያውቁ ሰዎች ፊት የፕራይቬታይዜሽን ሃሳብ ሲቃወም መስማት ያሳፍራል።
በግሉ ሴክተር የሚሳተፉ ድርጅቶች እንዴት ማህበረሰቡን በተሻለ ሁኔታ ማገልገል እንደሚችል እንመልከት። የድርጅቶች መመስረት ለህብረተሰቡ ጥሩ አገልግሎት ለመስጠት ነው እናም መልካም አገልግሎታቸው የነሱ መለኪያ መሆን አለበት።
የሚከተለውን ምሳሌ እንመልከት።
በመንግስት የመንጃ ፍቃድ ማረጋገጫ ፅህፈት ቤት ውስጥ ሰራተኞች ደመወዝ የሚከፈላቸው ቢሆንም የምስክር ወረቀቱ በትክክል ስለመሰጠቱ የማይጨነቁ ብዙ ሰራተኞች ሊኖሩ ይችላሉ። በርግጥ አንዳንድ ሰራተኞች የመንጃ ፍቃድ እንዴት እንደሚሰጥ እንዳለበት ጥንቃቄ ሊኖራቸው ይችላል፣ ነገር ግን ሌሎች ደግሞ ለግል ጥቅማቸው የሚኖሩም ኣይጠፉም። የምስክር ወረቀቱ ስለዚህ ብቃት ለሌላቸው አሽከርካሪዎች ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች በቀላሉ ሊሰጥ ይችላል። በዚህ ምክንያት ብዙ ጉዳቶች እና አደጋዎች በመንገድ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ ማለት ነው። ማንም ለዚህ ሃላፊነት አይወስድም፣ መንግሥት ነው መውሰድ ያለበት። ብዙ መንግስታት ግን ፣እንደ ኤርትራ መንግስት አይነት፣ ለድርጊታቸው ተጠያቂ ስላልሆኑ ፣ ጉዳቶች እና አደጋዎችን ችላ ብለው ያልፉታል።
የግል ኩባንያዎች ኣገልግሎት ስንመለከት ግን፣ አብዛኞቹ የኩባንያው ስም ስለሚያሳስባቸው የመንግሥትንና የዜጎችን አመኔታ ላለማጣት ሲሉ ፣ ስራቸዉን ኣጣርተው ለመስራት ይጥራሉ። መጥፎ ካደረጉ እና ከአቅም ማነስ የተነሳ አደጋዎች ቢበዙ፣ የብዙ ሰዎችን አመኔታ ያጣሉ እና በሌሎች ይተካሉ። ስለዚህ የግል ኩባንያ ከመንግስት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ይሞክራሉ ማለት ነው። ምክንያቱም ለስማቸው ስለሚያስቡ እና ጥሩ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛም ስለሆኑ ነው። በተጨማሪም፣ ልምድ እንደሚያሳየው የግል ኩባንያዎች የተሻለ አገልግሎት ይሰጣሉ። ከዚህ ባለፈም መንግስት ታክስ ይሰበስባል እና በዚህም የግል ባለሀብቶች መኖር ሃገር ይጠቅማል። ይሁን እንጂ ኢሳይያስ ሁሉም ነገር፣ በቁጥጥሩ ሥር ማድረግ ስለሚወድ የግል ኩባንያዎች በእሱ አመራር እንዲበለጽጉ አይፈልግም። ስለዚህም ነው ፣ የኤርትራ ባለሀብቶች በሌሎች የአፍሪካ አገሮች በስደት እንዲኖሩ የተገደዱት። የኢሰያስ መሪሕነት ኤርትራን ወደ ገደል እየከተተ መሆኑን ለመገንዘብ ጠለቅ ያለ ዕዉቀት አይጠይቅም።
ዲቮራ
Cookie | Duration | Description |
---|---|---|
cookielawinfo-checkbox-analytics | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookie is used to store the user consent for the cookies in the category "Analytics". |
cookielawinfo-checkbox-functional | 11 months | The cookie is set by GDPR cookie consent to record the user consent for the cookies in the category "Functional". |
cookielawinfo-checkbox-necessary | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookies is used to store the user consent for the cookies in the category "Necessary". |
cookielawinfo-checkbox-others | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookie is used to store the user consent for the cookies in the category "Other. |
cookielawinfo-checkbox-performance | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookie is used to store the user consent for the cookies in the category "Performance". |
viewed_cookie_policy | 11 months | The cookie is set by the GDPR Cookie Consent plugin and is used to store whether or not user has consented to the use of cookies. It does not store any personal data. |