Insightful articles and discussions to broaden your outlook.

My Perspective. Logo: A stylized representation of the company's name, with vibrant colors and modern design. Explore diverse perspectives on tech, culture, and lifestyle at My Perspective. Discover insightful articles and discussions to broaden your outlook.

ለምንድነው የኢትዮጵያ ቀረጥ እንደዚህ የበዛው

ኣንድ ኣንድ የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ለምንድነው የኢትዮጵያ ቀረጥ እንደዚህ የበዛው( check it here) ?። ምነው ከሁሉም ሃገር የበለጠ ሆነ ?  እኛን እንዳስገረመን፣ ለመሆኑ እናንተንስ ኣስገርሞ ይሆን ?  በሳዉዲ አረቢያና በሌሎችም ሃገሮች  ቀረጥ  ትንሽ ነው፣ ባደጉት ሃገሮችም ቢሆን  እንዲሁ  ነው  ተብለው ሲጠየቁ የሚመልሱት መልስ………………………………………..

አዎ ትክክክል ነው። እነ ሳዉዲ ኣረቢያ ነዳጅ ስላላቸው መንግስት ቀረጥ አያስፈልገዉም፣ሃብታሞች ናቸው። የኛ ሃገር ግን ደሃ ናት ። ባጀታችንን እንኩዋን በብድር ነው የምናካሂደው፣ መንግስታችን  ያለ ቀረጥ መኖር ኣይቻለዉም። ባደጉት ሃገሮችም እንደዛው ነው። ሃብታሞች ናቸው። ይሄ ነው ምክንያቱ ብለው ይመልሳሉ.።.

እንዲህ ኣልኩኝ >
ጋዳሚት ! ጋዳሚት ! (goddamnit!)ባገኛቸው ኖሮ እንዲህ  ብየ በመለስኩላቸው ነበር።

ከላይ የተጠቀሱት ሃገሮች ሃብታም የሆኑት ቀረጥ ስለማያስከፍሉ  እኮ ነው። ኣየህ በመጀመሪያ ህዝባቸዉን ሃብታም ያረጋሉ፣ ቀረጥ ያጎድላሉ ፣ህዝቡ ሃብታም ከሆነ። እሚበላዉን ሲያገኝ፣ ሃሳቡ ፈታ ሲል ፣  ኣጠገቡ ያለዉን ተፈጥሮዋዊ ሃብት ማየት ይጀምራል። ኣይኑ ይከፈታል  ማለት ነው። ከዛም መተጣጠፍ ይጀምራል ፣ በስተመጨረሻውም  እንቅስቃሴ ሲበዛ፣ ስራም እየተፈጠረ ሄዳል። ይሄ ነው ህዝቡን ሃብታም የሚያረገው። ሰማህ ወዳጄ ፣ የ ኣለኝን መንፈስ  (የ I am rich sprite)  በህዝቡ መካከል ወይም ውስጥ መፍጠር ኣስፈላጊነት ኣለው።  ፣ በመጨረሻም ህዝቡ ሃብታም ሲሆን መንግስትም ያለጥርጥር ሃብታም ይሆናል ማለት  ነው።  ይህን የኣለኝን መንፈስ ፈጥሮ፣ ሰው እንዲንቀሳቀስ ማድረግ እንጂ  ህዝቡን ድሃ ኣድርጎ፣ እየቆዘመ እንዲኖር ማድረግ ጥቅም የለዉም ።

ገንዘብ የሌለው ሰው እና ያለው ሰው እንዴት ነው የሚያስበው። ያለው ሰው ሁልጊዜም ባለው ተጠቅሞ ሌላ እንዲኖረው ይጥራል። የሌለው  ደሞ ሁሌም ስለማጣቱ እያሰበ ይቆዝማል። በድህነት ላይ ሌላ ድህነት ይጨምራል (the law of attraction should be considered here)።  ሎተሪ እንኩዋን ለ ሃብታም ነው የሚደርሰው ሲባል ሰምተው ያዉቃሉ? እስኪ ለምን እንደሆነ ይመርምሩ። ያለው ግን ሁሌም ያመሰግናል። እንደሚሉት ደሞ፣ እንግዜአብሄርም ማደሪያዉን የሚያደርገው በዚያው ነው፣ በነ ኣመስጋኞቹ ቤት። በ ረጋሚዎቹ ቤት እማ አይመቸውም።

ለነገሩ መንግስት  በቅንና  ሃላፊነት በሚሰማው መንገድ ሰፊዉን ህዝብ ከድህነት ለማዉጣት እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። መንግስት ህዝቡን ሆነ ብሎ ይጎዳል ማለት አይቻልም። ነገር ግን ዘዴዉን መቀየር ኣለበት፣ ለዉጥ የሚያመጣ ዘዴ መጠቀም ኣለበት እንጂ፣ እንደዱሮው መደጋገም ዋጋ የለዉም።  በሚኒሊክ ጊዜ የነበረን የቀረጥ ኣሰባሰብ  መድገም ለዉጥ ሊያመጣ ኣይችልም። አዎ መንግስት በሳንሳዊ የኣሰራር ዘዴ እየተመራን ነው ማለቱን ትቶ የሚያዋጣዉን ማድረግ ይሻለዋል ለማለት ነው። ሳይንስ ስንት ዉሸት ነው ያለበት?  እግዚአብሄር ይቁጠረው  የሳይንስን ዉሸት።  ባረጀው ባፈጀው ዘዴ መስራቱን ትቶ በሚዋጣው መንገድ ቢጓዝ  ለውጥ ሊገኝ ይችላል። የ ኣስተሳሰብ  ፓራዳይም ሽፍት ያስፈልጋል ማለት ነው። ድሮም መቆዘም ነው ኣሁንም ዘ ሴም ነው ኣለ ፈረንጁ። የድሮን በመድገም ለዉጥ ኣይመጣም።  ህልም ብቻ ሆኖ ነው የሚቀረው።

ስለዚህ ነው ከባቢህን ማየት የሚያስፈልገው ። አከባቢዉን አገናዝቦ ፣ ባለው ክዉንነታዊ ሁኔታ ተመርኩዞ ቢሰራ ፣ ዉጤትን ለማምጣት ይቻላል። የሳይንስንም እዉቀት (facts የምንላቸዉን )  ኣዙሮ መመልከት አስፈላጊነት ኣለው። ዝምብሎ እንደመጽሃፉ ገለጻ ከሆነ እንዲህ ነው ከማለት ይልቅ ፣ መጽሃፉን  መመርመር ያስፈልጋል።  የሚጠቅመዉን ወስዶ የማይጠቅመን መተው የግድ ነው.።

ሳይንስማ ሁሉም ትክክል ቢሆን የት በደረስን ነበር። ብዙው ነገር ለ ፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ የሚነገር ወይም የሚያስተምሩት እንደነበር ኣሁን ኣዉቀናል። ስለዚህ የራሳችንን ግንዛቤ በ ቀደምትነት ማሰለፍ ኣለብን።

ድሮ መሬት  መሃከሉዋ በጣም ሙቅ ነው ይሉን ነበር። ዛሬ እንደተማርነው ግን መሬት ክፍት (hollow) መሆኑዋንና፣ የተለያዩ ከተሞች  በከርሰ ምድሯ ዉስጥ እንዳሉ ተምረናል፣ የሰው ዘርም በዉስጡ እንደሚኖር አዉቀናል። እነ ኣጋርታእነ ሻምባላ የተባሉ ከተሞች እንዳሉ አዉቀናል።እድሜያችንን ሙሉ ሲያታልሉን ነው የኖርነው። ለዛ ነው ሳይንሳዊ መጽሓፉን በጠቅላላው ከመከተል፣ መመርመር ተገቢ ነው የምንለው። አንድ አንዱ ሆነ ተብሎ ማደናገሪያ እንዲሆን ተብሎም የሚጻፍም ኣለ።  የምድር ከርስ ሙቀት ከጸሃይ ይበልጣል ብለው እንዳስተማሩን ማለት ነው።

Challenge (ጠቅላላ እዉቀት) : በ ሰሜን ፖል እና በ ደቡብ ፖል ማን ኛዉም ሰው ሰራሽ ሳተላይት ማለፍ የተከለከለ ነው። በዚህም የተነሳ ሳተላይት ወ ደህዋ ሲመጥቅ በ 28 ድግሪ አጋድሎ ነው የሚዞረው። ወደ ፖሎቹም ዳታ(data) መሰብሰብ ኣይቻለዉም።፣  በ ፖል ኣከባቢ የጂፔኤስ ኣገልግሎት እንኳዋን አይሠራም። የማንኛዉም ኣይነት ኣዉሮፕላን እንኩዋን በ ሰሜን ፖልና በ ደቡብ ፖል እንዲበር አፈቀድለትም፣ ለምን ይመስሎታል ? ይመርምሩ ፣ በምድራችን ላይ ብዙ ሚስጥሮች አሉ፣ ፈልጎ ማወቅ ደሞ ፋንታዎ ነው።

በኣጭሩ ለማለት የተፈለገው ፣ ህሳቤያችን   Paradimeshift ያስፈልገዋል. We need to change our thinking; we need to shake it in order to come up with a different result. እውቀትንና  intuitionን ኣጋብቶ በጥምር መጓዋዝ ተመራጭነት አለው እያልን ነው።

ማስታወሻበ ጎግል ዉስጥ Agartha city ብለው ቢጽፉ ምድራችን በሆዱዋ ዉስጥ ስንት ከተማዎች እንዳሉዋት ማውቅ ይችላሉ። ወይም መጽሃፍቶችን በማንበብ ምድር ሆሎው ፣ ክፍት እንደሆነች ማወቅ ይቻልዎታል። ይህን መጽሃፍ  መጀመሪያ እንዲሆኖት ያንቡት፣  ቴሎስ

ኪንግ

LET’S KEEP IN TOUCH!

አዳዲስ ጽሁፎች እንዲደርስዎ ይመዝገቡ

የንግድ ማስታወቂያዎችን አንልክም ።

A call-to-action!

Welcome to Our site! Explore The Omo Valley Communities and Learn About Their Current Situation