ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ በአፍሪካ-ሩሲያ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጉዳያቸውን ለማቅረብ እድል ባገኙበት ወቅት ሁሉም አይነት የግብርና ምርቶች እንዳላቸው እና ፣ ገበያ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል። ኣዋቂ እና ጤናማ ፕሬዚዳንት ስለሚመለከታቸው ጉዳዮች ይጨነቃሉ። እድሉን ተጠቅመዉታል። በተመሳሳይ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የራሳቸውን ጉዳይ ጠቅሰዋል።
ኢሳያስ ግን የእሱ ጉዳይ ያልሆነውን፣ እሱ የማይመለከተውን ሁሉ ተናግሯል። አይኖችህን ከሽልማትህ ላይ አኑረው ይባላል። እሱ ግን እንደ እንድ የፖለቲካ አክቲቪስት፣ ኣቶ ፑቲን ስለ ምዕራቡ አለም ምንም አይነት እውቀት እንደሌለው ፣ ኢሳያስ ለፑቲን የዓለምን ታሪክ ሲያብራራለት ታይቶዋል። የሚገርመው የምሚያብራራው ታሪክ ከፌስቡክ የሰበሰበው እውቀት መሆኑና ፣የማነ ማንኪ በምሳ ወይም በሻሂ እረፍት ጊዜው ያቀበለው እውቀት መሆኑ ነው።
ኢሳያስ ሲያብራራ። እንደዚህ የሚያስበው ፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች የተሻለ ነገር እንዲኖራቸው ስለሚመኝ ነው ብሏል። ጂብ ወደ ሌላ ሀገር ሄዶ ቆዳ ኣንጥፉልኝ ኣለ ይባላል። ኢሳያስ እራሱን እንኳን መመርመር የማይችል ወይም የማያውቅ ሰው ነው። ኤርትራ በሰው መብት ረገጣ የምትታመስ ሃገር ፣ ህዝቦቿ በየኣቅጣጫው የሚሰደዱ ሆነው ሳለ፣ ኢሳያስ እንዲህ ብሎ ማሰቡ፣ የስነ አእምሮ ችግር ወይም ህመም እንዳለበት ያሳየሃል። ኤርትራ ጎልማሶች ብቻ ሳይሆኑ፣ ህጻናት እንኳን የሚታሰሩባት ሀገር ነች።
ከሁሉ የሚከፋው ደሞ ኤርትራ ለሩሲያ ገበያ የምታቀርበው፣ የምትሸጠው የግብርና ምርት የላትም፣ ወይም ሩሲያ የምትፈልገው ነገር ኤርትራ ውስጥ አይሰራም። ሌላ ታዲያ ምን መናገር ይችላል?
ለበለጠ ማብራሪያ የሚከተለዉን ያንብቡ፣
ተመልከት፣ ፑቲን ኣንድ ሞኝ ሰው የሚመለከት ሰውን ይመስላል። ኢሰያስ በእርጅናው ምክንያት ሃሳቡን ሲደጋግም ይታያል።ስንት ጊዜ #this war is not Russia war, this war is between NATO and Russia.# ኣለ፣ ይቁጠሩት እስኪ። ፑቲን በሌላ በኩል፣ በምናቡ እንዲህ ሲል የሚጠይቅም ይመስላል። #ለምን ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ኤርትራን ለቀው ወደ ውጭ አገር እንዲኖሩ ተገደዱ ብሎ የሚጠይቅም ይመስላል።# ለዚህ የሚሆን መልስ ኢሳያስ ጋር በጭራሽ ኣይገኝም። እራሱን የማያዉቅ ሰው እንዴት እንዲህ ያለዉን ነገ ሊያዉቅ ይችላል ? ኢሳያስ በ ERTV ላይም ተመሳሳይ ንግግር ያደርግና፣ ተቃራኒውን ደሞ መሬት ላይ ያደርጋል። ኢሳያስ ሃገር የማስተዳደር አቅሙ በጣም ትንሽ ነው። እሱ እራሱን የሚያየው፣ ብልህ ሰውና ባለእዉቀት እንደሆነ ነው። ትንሽ ኣእምሮ ያለው ሰው ደሞ፣ ሌሎች ሰዎች ጥያቄዎችን መጠየቅ ወይም መታዘብ የሚችሉም ኣይመስለዉም ። ሁሌም እያታለለ መኖር የሚችል ይመስለዋል። በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ባለሙያዎች ከሃገር እያባረረ ተሰልብጦ ፣ ተማሪዎችን ለማሰልጠን እርዳታ መጠየቁ ፣ ፑቲንንም ያስደምመው ይሆናል። ኢሳያስ እውነት የጎደለው፣ የእምሮ ህመምተኛ፣ ምንም ነውር የማያዉቅ እና ሞራል የሌለው ሰው ነው።
በዚህ ቪዲዮ የሰጠው ንግግር፣ አንድ የመዋዕለ ሕፃናት ተማሪ ለአንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር ስለ ዓለም ፖለቲካ እያስተማረ ያለ ይመስላል!
ኢሳያስ ህይወቱን በሙሉ በትግል ስም፣ በማይረባ ነገር ጊዜውን ያሳለፈ ሰው ነው። የባከነ ኑሮ ነው የኖረው። የሃይለስላሴ መንግስት በኤርትራውያን ላይ ያደርግ የነበረዉን አረመኔያዊ ድርጊት ለመከላከል ወደ ጦር ሜዳ የገባ ሰው ሆኖ እያለ፣ ከ30 ዓመታት ትግል በኋላ ግን የነጻነት ጊዜ እየተባለ በሚጠራው ወቅት፣ ከኃይለሥላሴ መንግሥት የባሰ ግፍና በደል በኤርትራዊያን ላይ ፈጽሟል። በተናገረው ነገር የማይኖር፣ እምነት የማይጣልበት እና ዋጋ የሌለው ሰው ነው። ስለ ኤርትራ የበለጠ ለማወቅ ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ፡
Leaks from Eritrea, Africa’s North Korea
Cookie | Duration | Description |
---|---|---|
cookielawinfo-checkbox-analytics | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookie is used to store the user consent for the cookies in the category "Analytics". |
cookielawinfo-checkbox-functional | 11 months | The cookie is set by GDPR cookie consent to record the user consent for the cookies in the category "Functional". |
cookielawinfo-checkbox-necessary | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookies is used to store the user consent for the cookies in the category "Necessary". |
cookielawinfo-checkbox-others | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookie is used to store the user consent for the cookies in the category "Other. |
cookielawinfo-checkbox-performance | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookie is used to store the user consent for the cookies in the category "Performance". |
viewed_cookie_policy | 11 months | The cookie is set by the GDPR Cookie Consent plugin and is used to store whether or not user has consented to the use of cookies. It does not store any personal data. |