Insightful articles and discussions to broaden your outlook.

My Perspective. Logo: A stylized representation of the company's name, with vibrant colors and modern design. Explore diverse perspectives on tech, culture, and lifestyle at My Perspective. Discover insightful articles and discussions to broaden your outlook.

እንዴት በአዲስ አበባ የሆቴል ዋጋ እንደዚህ ሊንር ቻለ?

በ ኢትዮጵያ የ ሆቴሎች እና የ ሎጅ ማደግ በግርድፉ ሲታይ አስደሳች ነው።  ደረጃዉን የጠበቀ ሆቴል በመኖሩ ከየአገሩ ለሚመጡ ቱሪስቶች ማስተናገጃ ይጠቅማሉ። ትንሽ ግር የሚያሰኘው ግን የ አዲስ አበባ ሆቴሎች ዋጋቸው ከ ኣዉሮፓ ሆቴሎች ጋር ተመጣጣኝ ዋጋ ማስከፈላቸው ነው። በአዉሮፓ ትንሽ የሚባለው ዋጋ 50 ዶላር ይደርሳል፣ ይህ ዋጋ በኣዲስ አበባም እንደዚያው ነው፣። ይገርማል እንዴት በአዲስ አበባ የሆቴል ዋጋ እንደዚህ ሊንር ቻለ ነው ጥያቄው።

በ አዉሮፓ የሆቴሎች ዋጋ ከፍ ቢል ምክንያት ኣለው። የሆቴል ባለቤቶች ለ ሰራተኞቻቸው የሚከፍሉት ደሞዝ ከፍ ያለ ስለ ሆነ ነው፣ በመንግስት በወጣ አዋጅ ምክንያት ፣ ዝቅተኛ ደሞዝ 3500 ዶላር በመሆኑ፣ ለሰራተኛ የሚከፍሉት ደሞዝ ከፍ ያለ ነው። ለ ጥጽዳት ሰራተኛ የሚከፈለው ደሞዝ ይህ ነው። በዚህ የተነሳ እናም በሌሎች ምክንያቶች የሆቴል ዋጋ ዉድ ይሆናል ማለት ነው። ምክንያታዊ ነው ። 50 ዶላር መክፈል ለማይችል ሰው ደሞ በ ሆስቴሎች ና በ ባክ ፓከርስ ከዚህ ያነሰ ዋጋ በመክፈል ይገለገላሉ። ስለዚህ ዋጋው ምክንያታዊ ነው.።

ታዲያ የኢትዮጵያ ሆቴሎች ምን ያህል ወጪ ቢኖራቸው ነው ከ ኣዉሮፓ እኩል የሚያስከፍሉት። ለነገሩ ከ ኣዉሮፓ ሆቴሎች ስንወዳደር እኩል አገልግሎት ነው የምንሰጠው ፣ ሆቴላችን ኣለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ ነው ሊሉ ይችላሉ። ማስከፈሉንስ ያስከፍሉ ፣  ነገር ግን የሰራተኛ ደሞዝ በ ኣዉሮፓዊያን ሆቴሎች ልክ ሊከፍሉ ይገባል። ይህንን መቆጣጠር ያለበት ደሞ መንግስት ነው።   የሰራተኞች ደሞዝም አለም ኣቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ ሆኖ በሆቴሉ የገቢ ምንጭ ልክ ሊሆን ይገባል ። ኣለበለዛ ርካሽ ጉልበት ተጠቅሞ ሃብት ማግበስበስ ይሆናል። ይሄ ደሞ ህጋዊ ኣደለም። የሰራተኛ መብት የሚጠብቅ ኣይደለም። ባለሃብቱ ያለአግባብ ፣ ምክናታዊ ባልሆነ ሁኔታ ገቢ እያስገባ፣ የማይመጣጠን ደሞዝ ለሰራተኞቹ ከከፈለ ባርነት ነው የሚሆነው።   ሰው ባገሩ እንዴት ባሪያ ይሆናል።

ሆቴሎች ለሰራተኞቻቸው ተመጣጣኝ ደሞዝ መክፈል ይገባቸዋል። መንግስት ይህንን መቆጣጠር ይገባዋል። መንግስት ለህዝብ የቆመ መንግስት ከሆነ፣  አንዱ ዜጋ የሌላዉን ዜጋ ጉልበት በርካሽ ተጠቅሞ ሃብት ሲያከማች ዝም ከማለት በጉዳዩ ዉስጥ ገብቶ የሰራተኛ መብት ማስከበር ይጠበቅበታል።

LET’S KEEP IN TOUCH!

አዳዲስ ጽሁፎች እንዲደርስዎ ይመዝገቡ

This field is required.

የንግድ ማስታወቂያዎችን አንልክም ።