Insightful articles and discussions to broaden your outlook.

My Perspective. Logo: A stylized representation of the company's name, with vibrant colors and modern design. Explore diverse perspectives on tech, culture, and lifestyle at My Perspective. Discover insightful articles and discussions to broaden your outlook.

የኤርትራ መንግስት በአውሮፓ ውስጥ ባሉ ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ የፈቀደዉን የሚያደርገው በአስተርጓሚዎች እና በስለላ መረቡ አማካኝነት ነው።

ትርጉም ትግርኛ

Translation française
English Translation

የኤርትራ መንግስት በአውሮፓ ውስጥ ባሉ ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ የፈቀደዉን የሚያደርገው በአስተርጓሚዎች እና በስለላ መረቡ አማካኝነት ነው።


በአውሮፓ የኤርትራ መንግስት ወንጀል በየቦታው እየተጋለጠ መሆኑን መስማት በጣም ደስ ይላል። ነገሮች እየተለወጡ ነው ፣የኤርትራም ሁኔታ ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ተብራርቷል ሊባል ይቻላል። በተለይ የአስተርጓሚዎች ተብዬዎቹ በስደተኞች ላይ የሚያወርዱት ጉዳት። ይሁን እንጂ እንደዚህ አይነት ወንጀሎች በኤርትራ ስለላ መርበብ ሊሰሩ እንደሚችሉ አውሮፓውያን አስቀድመው አለማሰባቸው የሚያስገርም ነው። ገና ከጅምሩ ለእነዚህ ነገሮች ትኩረት ቢሰጡ ኖሮ ብዙ ሐቀኛ ስደተኞችን መርዳት ይችሉ ነበር። የአውሮፓ የኢሚግሬሽን ቢሮዎች በራሳቸው ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ከመንግስታቸው የስለላ ቀለበት አለመከላከላቸው ድክመት ነው።

ዋናዎቹ ወንጀለኞች ኤርትራዊያን ተርጓሚዎች ናቸው፣ በተጨማሪም በአውሮፓ ውስጥ ያሉ ብዙ የኤርትራ የስለላ ማህበረሰብ አባላትም ተጠያቂ ናቸው። የጥገኝነት ጠያቂውን ህይወት ለማበላሸት ረጅም ጊዜ ሲሰሩ ቢቆዩም፣ አሁን ግን ጊዜያቸው የደረሰ ይመስላል። ይህ ጉዳይ በስደተኞች ጽሕፈት ቤት ክብደት ባይሰጠዉም ፣ በተደጋጋሚ እንዲህ ዓይነቱን መረጃ ከበርካታ ዓመታት በፊት በተለያየ መንገድ ይደርሳቸው ነበር።


በሁሉም ጊዜያት እና ቦታዎች የቲያትር ስራዎችን አይተናል። የኤርትራ መንግስት አንዳንድ የአውሮፓ ፓርላማ አባላትን ኤርትራን እንዲጎበኙ ጋብዞ ነበረ። በመጨረሻም አንዳንድ የፓርላማ አባላት ተጋባዦች፣ የኤርትራ መንግስት ቴአትርን አምነው በስደተኞቹ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የጠየቁም ነበሩ።


የአዞ እንባ መሆኑ ነው እንጂ፣ የኤርትራ መንግስትስ ከስደተኞች ተጠቃሚ ስለሆነ፣ ስደተኞች እንዲኖሩ ይፈልጋል። እንዲኖሩ የሚፈልገው ለአገሪቱ የዉጭ ምንዛሪ ምንጭ በመሆናቸው ነው። መንግሥት ገንዘብ ለማግኘት ሌሎች መንገዶችን መመልከት አልቻለም። ይህ የሚያሳየው፣ የኤርትራ መንግስት መሪዎች ዜጎቻቸውን በማሰደድ እንደ ገንዘብ ማመንጫ በመጠቀም ፣ ስረአታቸዉን ለማስቀጠልና ለማቆየት የሚያደርጉት መላ መሆኑ ነው። የኤርትራ መንግስት ብዙ ስደተኞችን ወደ ስደት እንዲሄዱ ፍላጎቱ የሆነበት እንዱ ምክንያት ሰላዮቻቸውን በስደተኛ መልክ በቀላሉ እንዲልኩ ስለሚያስችላቸዉ እና ስደተኞች የገንዘብ ምንጭም ጭምር በመሆናቸው ነው። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎችን ይገድላሉ። የዉጭ ምንዛሬ ይሰበስባሉ፣ በተጨማሪም ተቃዋሚዎቻቸውንም ያደናቅፋሉ። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ስደተኞች ለኤርትራ መንግስት የዉጭ ምንዛሪ ማስገቢያ ዘዴ መሆናቸዉን ነው።

ስደተኞች ወደ አውሮፓ ከገቡ በኋላ ፣ በአውሮፓ ለረጅም ጊዜ የኖሩ የመንግስት ሰላዮች (የኤርትራ መንግስት ተላላኪዎች) የሆኑ ኤርትራዊያን፣ የመንግስት ደጋፊ ስደተኞችን በማገዝ የመኖሪያ ፍቃድና ከዛም ስራ እንዲያገኙ ይረዷቸዋል ። በሌላ በኩል መንግሥትን የሚቃወሙትን ደግሞ ሥራ እንዳያገኙ ወይም እንዳይሠሩ ለማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ። በዚህ ምክያትት ነው የበዛው ኤርትራዊ ስደተኛ አውሮፓ ከገባ በሁዋላ መንግስትን ከመቃወም ፈራ ተባ የሚለው። ይህ ካልሆነ ግን በኤርትራ መንግስት የስለላ መረብ በሚያደርሰው በርካታ ክፋቶች ይሰቃያሉ። በአንዳንድ ካንቶኖች የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘትና ሥራ ማግኘት በኤርትራ መንግስት ኔትወርኮች፣ ተርጓሚዎች እና ሌሎች የረጅም ጊዜ ነዋሪዎች ማህበረሰብ በኩል ስለሚደገፍ።

ሌላው መንግስት የሚፈጽመው አስጸያፊ ተግባር እያንዳንዱን ኤርትራዊ ስደተኛ በሰላዮቹ መረብ መከታተል ነው። አጥንቶ መረጃውን እዚ ወይም ኤርትራ ውስጥ ላለው ለአለቃቸው ማሳወቅ ነው። ለምሳሌ መንግስትን የሚቃወም ኤርትራዊ ስደተኛ ስራ ቢያገኝ፣ በዝምታ ተከታትለው የሚሰሩበትን ቦታ እና ድርጅቱን በማጥናትና ከዚያም ባላቸው መርበብ እናም ጉቦ በመክፈል፣ ያሰው ከስራው እንዲፈናቀል የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ። ይህ የኤርትራ መንግስት እጅግ አስጸያፊ እና ድብቁ ሴራ ነው።

በዚህ ወንጀል ከመንግስት ጎን ሆነው የሚሳተፉ የኤርትራ ተላላኪዎችም በተለያዩ ስልቶች እና የማታለያ ዘዴዎች ነው እንዲሳተፉ የሚገደዱት። አንዳንዶቹ በደካማ ጎናቸው፣ አንዳንዶቹን በሆዳቸው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በማስገደድና በማስፈራራት ይጠቀሙባቸዋል። በአውሮፓ ከ30 ዓመታት በላይ የኖሩት አብዛኞቹ ኤርትራዊያን ስደተኞች ኤርትራ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ በርካሽ መሬት ወይም አፓርታማ እንዲገዙ ከተሳቡ በኋላ፣ እናም ከተወሰነ አመት በኋላ እነዚህኑ ኢንቨስትመንቶች እንደ መያዣ በመጠቀም መንግስት እነኚህን ሰዎች ለማስገደድ ይጠቀምባቸዋል። አንዳንዶች ደሞ ፣ አደጋ ላይ ሊሆኑ የሚችሉ የቤተሰብ አባላት ሊኖራቸው ይችላል እና ስለዚህ በቀላሉ የመንግስትን ትዛዝ ይከተላሉ። ስለዚህ በመንግስት ክፉ ስራ የሚተባበር ወይም የሚሳተፍ ዜጋ በተለያዩ ምክንያቶች መሆኑ ነው።

ኤውሮጳውያን የኤርትራን መንግስትን ሴራ ብትክክል ስላልተረዱ ግን ፣ ብዙ እዉነተኛ ስደተኞች ተበድለዋል እስከዛሬም አሁንም እየተበደለ ነው ሊባል ይቻላል፣

ዲቮራ (የብዕር ስም)

LET’S KEEP IN TOUCH!

አዳዲስ ጽሁፎች እንዲደርስዎ ይመዝገቡ

የንግድ ማስታወቂያዎችን አንልክም ።

A call-to-action!

Welcome to Our site! Explore The Omo Valley Communities and Learn About Their Current Situation