የሰው ልጅ መብቶች ቀለል ባለ መልኩና በአጭሩ ህብረተሰቡ በሚረዳው ቋንቋ ተጽፎ ቢቀርብለት፣ ምናልባትም ብዙው ሰው የሌላዉን ሰው መብት እንዴትና እንደምን አድርጎ ማክበር እንዳለበት ይረዳው ይሆናል በሚል እሳቤ፣ የሚከተለዉን የፈረንሳይ ሃገር የሰው ልጅ መብት የሚያስከብረዉን አዋጅ ወደ አማርኛ እንደሚከተለው ተርጉሞ ለማቅረብ ተሞክሯል። በአጭርና ግልጽ በሆነ ቋንቋ፣ የሰው ልጆች መብት እስከምን ድረስ እንደሆነ፣ በትምህርት ቤት ቢሰጥ፣ ህብረተሰቡ የሌላዉን ሰው መብት እንደራሱ አድርጎ ማክበር ቢለማመድ፣ ምንኛ ፍቅር በነገሰ ነበር። በተለይ በአፍሪካ ዉስጥ ብዙ ሰዎች ላገራቸው ያሰቡ እየመሰላቸው፣ ከህግ ዉጭ በሆነ መንገድ፣ በሌሎች ዜጎች ላይ፣ ይህ መሆን አለበት ፣ ያነው መሆን ያለበት፣ ወይም እኔ ነኝ ትክክለኛ በማለት ሌላኛው ላይ ጥቃትን ያደርሳሉ። ይህ ደሞ ህግና ስረዓትን የጣሰ በመሆኑ፣ በህግ ሊከለከል ይገባል። በይመስለኛል ሃሳብን ማንሸራሸር ፣ ሁሉኑም አዉቃለሁ በሚል ግንዛቤ፣ ወይም በእውቀት ማነስ የተደገፈ አመለካከት የሌሎች ሰዎችን መብት ስለሚጥስ ፣ ባልተረጋገጠ አመለካከት ህብረተሰብን ማነሳሳት፣ ሃገርንና ህዝብን ስለሚጎዳ፣ ሳናረጋግጥ እርምጃ ከመዉሰድ ወይም ከመናገር እንቆጠብ። አንድ ሰው በእራሱ ላይ እንዲሆን የማይፈቅደዉን ነገር፣ በሌላኛውም ላይ እንዳይፈጸም መከልከሉ እራስን እንደ መከላከል ይቆጠራል። ህብረተሰብን ማስተዳደርም ቢሆን፣ ህግን ተመርኩዞ ሲሆን፣ ስጋትና ፍርሃትን ይቀንሳል።
በተጨማሪም፣ መብቱ የተከበረለት ሰው ሃግሩን ትቶ ወደ ስደት መሄድን አይመኝም ፣ ህግ ያለው ህብረተሰብም፣ በባለሥልጣናት በዘፈቀደና በማን አለብኝነት አይተዳደርም። መብቱንና ግዴታዉን ጠንቅቆ የሚያዉቅ ህብረተሰብም ላገዛዝ ይመቻል። ባለስልጣናቱም የስልጣን ጊዚያቸዉን በደስታና በሰላም ስለሚያስተዳድሩ ፣ የስልጣን ጊዜያቸው የሰመረ ይሆናል። ብዙም ጣጣም አይኖርባቸዉም።
መብቱንና ግዴታዉን በሚገባ የሚያቅ ህብረተሰብ፣ የረቀቀ ህግ ያለዉና ህጉንም ተግባራዊ የሚያደርግ ሃገር ፣ የዉጭ ጣልቃገብነት ቢኖርም እንኳ፣ በህጉ መሰረት መከላከል ይችላል። የሌላ ሃገር ዜጎችም ቢሆኑ፣ የሃገር ዉስጥን ህግ አክብረው እስከኖሩ ድረስና፣ ህብረተሰቡን ሊጎዳ የሚችል ነገር እስካላደርጉ ድረስ፣ በፈቀዱትና በወደዱት ቦታ መኖር ተፈጥሮዋዊ መብታቸው ሊሆን ይገባል። እግዜአብሄር በፈጠረውና ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ በዘረጋው መሬቱ ፣ የሰው ልጅ ጥልቅ ብሎ፣ ሌላኛዉን የእግዜአብሄር ፍጡር፣ አንተ እዚህ መኖር አትችልም፣ ይሄ የኔ ምድር ነው ብሎ ማለትና ማሰብ፣ ስግብግብነት ብቻ ሳይሆን ድንቁርናም ነው። የሃገርን ኢኮኖሚ ከመጉዳት ባሻገር፣ የሰዉን ልጅ ተፈጥሮዋዊ መብትንም ይቃረናል። በምድር ላይ የሚኖር ፍጡር ሁሉ ጊዜያዊ እንጂ ዘላለማዊ ባለመሆኑ፣ በፍቅር፣ በመቻቻልና ፣ በመረዳዳት መኖር ተገቢ ብቻ ሳይሆን፣ ፈጣሪንም ያስደስታል።
The declaration of the rights of man and of the citizen (1789)
The declaration of the rights of man and of the citizen (1789)
ከቻሉ ከላይ ያለውን ገጽ በአንድ ገፅ ያትሙ እና ሼር ያድርጉት።
Print the page above on one page and share it, I mean if you can…
Imprimez la page ci-dessus sur une page et partagez-la, je veux dire si vous le pouvez…
Cookie | Duration | Description |
---|---|---|
cookielawinfo-checkbox-analytics | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookie is used to store the user consent for the cookies in the category "Analytics". |
cookielawinfo-checkbox-functional | 11 months | The cookie is set by GDPR cookie consent to record the user consent for the cookies in the category "Functional". |
cookielawinfo-checkbox-necessary | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookies is used to store the user consent for the cookies in the category "Necessary". |
cookielawinfo-checkbox-others | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookie is used to store the user consent for the cookies in the category "Other. |
cookielawinfo-checkbox-performance | 11 months | This cookie is set by GDPR Cookie Consent plugin. The cookie is used to store the user consent for the cookies in the category "Performance". |
viewed_cookie_policy | 11 months | The cookie is set by the GDPR Cookie Consent plugin and is used to store whether or not user has consented to the use of cookies. It does not store any personal data. |